Children categoriesEPHA Implements Stay at Home AdviceAs of 31st of March 2020, most staff members of the Ethiopian Public Health Association (EPHA) secretariat are off workplace and stayed-at-home as measure for prevention of COVID-19 pandemic.
ከሙያ ማኅበራት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ መጋቢት 16 ቀን 2012 ዓ.ም. የኮሮና ቫይረስ በሽታ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመግታት እየተደረገ ያለውን ሀገራዊ ምላሽ /National response/ ለማገዝ የጤና ሙያ ማኅበራት የተቀናጀ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ይገኛሉ። በአሁኑ ወቅት በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሎም በኢትዮጵያ አሳሳቢ እና ዋነኛ የሕብረተሰብ ጤና ስጋት የሆነውን የኮቪድ-19 በሽታ ወረርሽኝ ለመከላከል ብሎም ለመቆጣጠር በተለያዩ አካላት በተለይም በመንግስትና በሙያ ማህበራት ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴ በመደረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ ሲቪል የማሕበረሰብ ድርጅቶች አካል የሆኑት የጤና ሙያ ማሕበራት ተቀናጅተው ህብረተሰቡ ለበሽታው እንዳይጋለጥ ሳይንሳዊ /scientific/ እና በመረጃ ላይ የተመሰረተ /evidence based/ በሆነ መንገድ መንግስት እየወሰደ ያለዉን የመከላከልና የመቆጣጠር እርምጃ በመርዳት ላይ ይገኛሉ፡፡ ለአብነት ያህል ካለፈዉ ሳምንት ጀምሮ ለጤና ባለሙያዎች ስልጠና በመስጠት ላይ እንገኛለን፡፡ እንዲሁም የበሽታውን ምንነት እና መከላከያ መንገዶችን ለኅብረተሰቡ ለማድረስ ልዩ ልዩ መልዕክቶችን በማሳተም እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ቫይረሱ በሌሎች አገሮች እያደረሰ ካለው አስከፊ ቀውስ በመነሳት በጋራ እየሰራ የሚገኘዉ የሲቪል ማሕበረሰብ ድርጅቶች አካል የመከላከልና የመቆጣጠር ስራዉን በተሻለ ሁኔታ ለማቀናጀትና የተለያዩ አካላትንም ድርሻ ለመጠቆም ይህ መግለጫ ተዘጋጅቷል:: Work Place Interventions in Ethiopian Public Health Association (EPHA) on COVID-19 PreventionEPHA has performed the following activities in relation to COVID-19 prevention
It is believed that, other Governmental and Nongovernmental organizations will take a lesson from EPHA |