![]() Children categoriesለኢጤአማ አባላት በሙሉእንኳን ለ2015 ዓ.ም አዲስ አመት በሰላም አደረሰን እያልን መጪው ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የጤና እና የእድገት እንዲሆንልን እንመኛለን።ኢጤአማ
BRIEF MONTHLY NOTE ON THE STATUS AND TREND OF COVID-19 PANDEMIC MAY 2022 INTRODUCTION. This brief is focused on selected major national events during the five Epi-weeks of JUNE 2022 (30 MAY -3 JULY 2022) that include trend in newly reported cases, deaths, laboratory tests performed, CFR and % Test Positivity Rate. All figures are based on official government data (EPHI daily tweet notification. The CFR and % Positive rates are computed from the reported figures. The findings from MAY are compared with the preceding month of that of APRIL. Table 1. MONTHLY SUMMARY JUNE-MAY and APRIL
TABLE 2 SUMMARY OF WEEKLY REPORTED CASES JUNE 2022
የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር (ኢ.ጤ.አ.ማ) በሰሜን ወሎ ዞን በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው 5 ጤና ጣቢያዎች 2 ነጥብ 6 ሚሊዬን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
ማኅበሩ ከግሎባል አሊያንስ እና ፓካርድ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ልዩ ልዩ ለህክምና አገልግሎት መስጫ የሚውሉ መሳሪያዎችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ መኮንን በወልድያ ከተማ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ተገኝተው አስረክበዋል፡፡
ዳይሬክተሩ በጦርነቱ በጤና ተቋማቱ ላይ የደረሰውን ውድመት በስፍራው ተገኝተው በማጤን የሚያስፈልጋቸውን መሰረታዊ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የጤና ባለሙያዎች ከሥነ ልቦና ጫና ተላቀው ለማኅበረሰቡ የተሻለ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ማኅበሩ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
የተደረገው ድጋፍም ለሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ፣ አይዳ ፣ ደንሳ፣ ሮቢት እና አይና ቡግና ጤና ጣቢያዎች እንደሚከፋፈል ተገልጿል፡፡
በተመሳሳይ በዛሬው እለትም በደሴ ከተማ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
|