Who's Online

We have 87 guests and no members online

Rate this item
(0 votes)
የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር (ኢ.ጤ.አ.ማ) በሰሜን ወሎ ዞን በጦርነቱ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው 5 ጤና ጣቢያዎች 2 ነጥብ 6 ሚሊዬን ብር ግምት ያለው የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ 
 
ማኅበሩ ከግሎባል አሊያንስ እና ፓካርድ ፋውንዴሽን ባገኘው የገንዘብ ድጋፍ ልዩ ልዩ ለህክምና አገልግሎት መስጫ የሚውሉ መሳሪያዎችን ድጋፍ ያደረገ ሲሆን፤ የማኅበሩ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አለማየሁ መኮንን  በወልድያ ከተማ ግንቦት 8 ቀን 2014 ዓ.ም. ተገኝተው  አስረክበዋል፡፡ 
 
ዳይሬክተሩ በጦርነቱ በጤና ተቋማቱ ላይ የደረሰውን ውድመት በስፍራው ተገኝተው በማጤን የሚያስፈልጋቸውን መሰረታዊ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የጤና ባለሙያዎች ከሥነ ልቦና ጫና ተላቀው ለማኅበረሰቡ የተሻለ የህክምና አገልግሎት እንዲሰጡ ለማስቻል ማኅበሩ ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
 
የተደረገው ድጋፍም ለሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ፣ አይዳ ፣ ደንሳ፣ ሮቢት እና አይና ቡግና ጤና ጣቢያዎች እንደሚከፋፈል ተገልጿል፡፡ 
 
በተመሳሳይ በዛሬው እለትም በደሴ ከተማ ርክክብ የሚፈጸም ይሆናል፡፡